Noticias

ለአንቺ በእርግዝናሽ ወቅት ማወቅ ያለብሽ ሰባት ነገሮች።(የሐኪምሽ ምክር)

ለአንቺ
በእርግዝናሽ ወቅት ማወቅ ያለብሽ ሰባት ነገሮች።(የሐኪምሽ ምክር)

1. በ እርግዝናሽ ወቅት በቂ የሆነ የፅንስ ክትትል አድርጊ።

ማርገዝሽን ካወቅሽበት ቀን ጀምሮ ተገቢውን የእርግዝና ክትትል ማድረግ ይኖርብሻል ።
በክትትል ወቅትም አስፈላጊ የሆኑ የደም የሽንት የአልትራሳውንድ ምርመራ ማድረግ ይጠበቅብሻል::

2. አይረን እና ፎሊክ አሲድ መውሰድ አለብሽ ። ምክንያቱም ፎሊክ አሲድ በበቂ ከወሰድሽ የቀይ ደም ህዋስ እንዲመረት እና የደም ማነስ እንዳይከሰትብሽ ያደረጋል።

ፎሊክ አሲድ በበቂ ከወሰድሽ ሕፃኑ ላይ የ ነርቭ ዘንግ ክፍተት (Spina bifida) እንዳይከሰት ይከላከላል ።

ፎሊክ አሲድን የሚይዙ ምግቦች ፡- ብርቱካን ፣ ወይን ፣ ፓፓያ ጎመን ፣ሩዝ ፣ ባቄላ ፣ ስኳር ድንች ፣ እንቁላል ፣ ዳቦ ፎሊክ አሲድን ከነዚህ ውስጥ ማግኝት እንችላለን ፡፡

3. የደም አይነትሽን ማወቅ ይጠቅምሻል ።የ የሚጠቅምሽም ባንቺ እና በ ልጅሽ የደም አለመመሳስል ምክንያት ፅንሱ ላይ የሚደርሰውን ጉዳት እንዳይደርስ እንድትከላከይ ይረዳሻል ::

በተለይ ያንቺ የደም አይነት ኔጌቲቭ የሚባለው ከሆነ

ለምሳሌ A negative, B negative, AB negative ወይም O negative ከሆነ የሾተላይ መከላከያ ወይም አንታይ ዲ (Anti – D) የሚባለውን መድሃኒት እርግዝናው ከታወቀ በ 7 ተኛ ወር ላይ እና ከወሊድ በኋላ በ 72 ሰአት ወሰጥ መውሰድ ይኖርብሻል።

4. ለህመም ማስታገሻ ተብለው የሚወሰዱ መድሀኒቶችን ያለ ሀኪም ትእዛዝ አትውሰጂ።

በተለይ በመጀመሪያዎቹ 16 ሳምንታት የእርግዝና ወቅት የህፃኑ ዋና ዋና የሚባሉ የሰውነት ክፍሎች የሚፈጠርበት ግዜ ስለሆነ ፅንሱ ላይ ጉዳት ያደርሳያደርሳል

5. በእርግዝና ግዜ የአተኛኘትሽን አስተካክይ።

በእርግዝና ወቅት መተኛት ያለብሽ በግራ ጎንሽ መሆን አለበት።
በግራ ጎንሽ ስትተኚ ወደ ፅንሱ የሚሄደውን ምግብ እና የደም ዝውውርን እንዲጨምር ያደርጋል:: በጀርባሽ የምትተኚ ከሆነ ግን በተቃራኒው ወደ ልጅሽ የሚሄደው ምግብ እና የደም ዝውውር ሊቀንስ ይችላል።

6. ምግብሽን ሳታበስይ አትመገቢ!

በእርግዝና የሚከለከሉ ምግቦች ብዙም የሉም ። እንደውም ጤናማ ከሆኑ(ማለትም የበሰሉ እና በንፅህና የተዘጋጁ) ከሁሉም የምግብ አይነት እናት እንድትመገብ ይመከራል ።
ጣፋጭ እና የ ታሽጉ ምግቦችን አታዘውትሪ።

7. በ እርግዝና ወቅት በቂ እና ጤናማ የሆነ ኪሎ መጨመር ይኖርብሻል።

ከእርግዝና በፊት ከምትመገቢው ምግብ ተጨማሪ ምግብ ያስፈልግሻል።
——
ዶር ፋሲል መንበረ
የሕጻናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር
ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ

admin

Compartir
Publicado por
admin
Etiquetas: noticias

Entradas recientes

Un Día Especial

Un día Especial En la aldea rural de Gambo, situada en una aislada zona de…

4 meses hace

Doce Años de valor y esperanza

12 Años Salvando Vidas en Etiopía: Un Viaje de Esperanza y Cambio Durante los últimos…

5 meses hace

Carta de Agradecimiento a la Fundació Occident

Carta de Agradecimiento a la Fundació Occident   Estimados miembros de la Fundació Occident, Quisiera…

5 meses hace

Congratulations Mekdes Daba, our New Health Minister

Congratulations Mekdes Daba, our new Minister of Health   Developing Story: Mekdes Daba Appointed as…

10 meses hace

Nuestro Plan para 2024

  Nuevos Objetivos para el Año 2024 1. Mejorar la infraestructura de seguimiento y supervisión…

10 meses hace